enfrit

Sustainability

የአንበሳ ጫማ አ/ማ የምርት ስነ-ምግባር ደንብ

አንበሳ ጫማ አ/ማ  እንደ ተቋም የዜግነት ግዴታውን በኃላፊነት የሚወጣ ድርጅት ከመሆኑ አንጻር በጫማ ማምረት ኢንዱስትሪ ውስጥ የበለድርሻ አካላትን  ሁለንተናዊ መብት በማስከበር መርህ ላይ ንቁ ተሳታፊ ነው። ለድርጅቱ፣ ለሁሉም ጫማ ምርት ግብአት አቅራቢዎቹ እና የድርጅቱን ስራዎች በኮንትራት ወስደው ለሚሰሩ ድርጅቶች እንደ መተዳደሪያ ደንብ የሚያገልግለውን ይህንን የምርት ስነ-ምግባር ደንብ አዘጋጅቷል። ይህን ደንብ በተግባር ላይ በማዋል ሂደት ወቅት አንበሳ ጫማ አ.ማ.  “ቀጣይነት ያለው መሻሻል” የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ይዞ ወደፊት የሚራመድ ሲሆን፣ አቅራቢዎችና በተቋራጭ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች በበኩላቸው የተሻሉ አሰራሮችን እንዲተገብሩ እና በአመራረት የሥራ ሂደቶቻቸው ላይ በሙሉ ቀጣይ መሻሻል ላይ በማተኮር እንዲሰሩ ያበረታታል።

 

 

Contact Information

Akaki Kality Sub-City, Woreda 02, House-No 202, Addis Ababa Ethiopia
marketing@anbessashoesc.com

Hot Line Phones